የኦሞ ቤዛ የህፃናት አገልግሎት ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ የሚተጋ የተለወጠ ትውልድ ለማፍራት ለዓመታት በደቡብ ኦሞ በታማኝነት ሲያገለግል ቆይቷል። ይህንን ስኬታማ ጉዞ ወደ ቀጣዩ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር፤ የራዕይ ማጋሪያ፣ የትብብር ጥሪ እና የመጽሐፍ ምረቃ መርሃ-ግብር አዘጋጅተናል። በዚህ ታላቅ መርሃ-ግብር ላይ እንዲገኙ በክብር ተጋብዘዋል።
የራዕይ ማጋሪያ እና የመጽሐፍ ምረቃ
ቀን፦ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (May 24th, 2026)
ሰዓት፦ ከቀኑ 8:30 እስከ 12:00 ሰዓት
ቦታ፦ አክላ (ACLA) ቤተክርስቲያን
አገልግሎቱ ፈጽሞ ብቻችንን የምንወጣው ተልዕኮ አይደለም። በጅማሬያችን ወቅት የኦሞ ተወላጆች በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድጋፍ ሲያደርጉልን ቆይተዋል። በአሁኑ ሰዓት ግን ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ስላለ የእግዚአብሔርን፣ የጓደኞቻችንን እና የአጋሮቻችንን ድጋፍ እንፈልጋለን።
የዚህ ታሪክ አካል መሆን ይፈልጋሉ? የእርስዎ ድጋፍ በደቡብ ኦሞ የህፃናትን ህይወት እንዴት እንደሚቀይር አብረውን ይከታተሉ።
አዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሰምብሊ (ACLA)
የእርስዎ ድጋፍ ይህንን ራዕይ ይበልጥ ለሚያስፈልጋቸው ህፃናት የእንክብካቤ፣ የትምህርት፣ የአምልኮ እና የተስፋ ማዕከል እንዲሆን ይረዳል።
በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ከራዕዩ ጎን ይቁሙ፤ መልዕክቱንም ለሌሎች ያጋሩ።




